ጥንታዊ እንግሊዝኛ

«ጎደስ ፌውሕ ኦንድ ቺሪቼየን ትወልቨ ዪውልደ።» («የአምላክ ነዋይና የቤተክርስቲያን፣ ፲፪ እጥፍ») በማለት ከሁሉ ጥንታዊ የታወቀው የእንግሊዝኛ ዓረፍተ ነገር፣ የ አሰልበርህት ህግጋት ( 594 ዓም)፣ ይጀምራል። ይህ በ1100 ዓም ግድም የተሠራ ቅጂ ነው።

ጥንታዊ እንግሊዝኛ (Englisc /ኧንግሊሽ/) በ እንግሊዝ አገር ከ440 ዓ.ም. ገደማ እስከ 1100 ዓ.ም. ያሕል የተናገረ ቋንቋ ነበር። ዛሬ ጀርመንዴንማርክ ከተባሉት አገሮች ፈልሰው በእንግሊዝ በተስፈሩት ሕዝብ የተናገሩበት ሲሆን የዘመናዊ እንግሊዝኛ ቀድሞ አይነት ነው። ሆኖም በቃላትም ሆነ በስዋሰው ከዘመናዊ እንግሊዝኛ በጣም ይለያል። ቅርብ ዘመዶቹ ጥንታዊ ፍሪዝኛ እና ጥንታዊ ሴክስኛ ናቸው።

ጥንታዊ እንግሊዝኛ በርካታ ተመሳሳይ ቀበሌኞች ነበሩት። በተለይ በስሜን እንግሊዝ የኖሩት የ አንገሎች መነጋገርያ በደቡብ ከኖሩት ከ ሴክሶች ትንሽ ተለያየ።

ከ800 ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ስሜኑ በ ቫይኪንጎች ስለተወረረ በንጉስ አልፍሬድ ጊዜ የሴክሶች ቀበሌኛ ይፋዊ ሁኔታ አገኘ። ቢሆንም የቫይኪንጎች ቋንቋ ኖርስኛ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ ጋር ዝምድና ነበረውና ከኖርስኛ አያሌው ቃላት ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ለምሳሌ የእንግሊዝኛ ቃላት sky /ስካይ/ (ሰማይ) leg /ለግ/ (እግር) እና they /ዘይ/ (እነሱ) የደረሱ ከኖርስኛ ነበር። በእንግሊዝ ኗሪዎች ቋንቋ (በጥንታዊ እንግሊዝኛ) እነዚህ ቃላት 'ሄዮቮን'፣ 'ሽያንካ' እና 'ሂዬ' ሆነው ነበር።

የተማሩ ሰዎች (መምህራን ወይም ቄሶች) በብዛት የ ሮማይስጥ ዕውቀት ስለነበራቸው ደግሞ ከሮማይስጥ ተጽእኖ አንዳንድ ቃላት የዛኔ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ንጉሥ አልፍሬድ እራሳቸው ብዙ መጻሕፍት ከሮማይስጥ አስተረጎሙ።

ኖርማኖች እንግሊዝን በ 1059 ከወረሩ ጀምሮ እንግሊዝኛ ከትምህርት ቤት ስለ ተከለከለ በየጥቂቱ ባሕርዩ እጅግ ተለወጠ።

በጥንታዊ እንግሊዝኛ እያንዳንዱ ስም የተወሰነ ጾታ (ወንድ፣ ሴት ወይም ግዑዝ) ነበረው። ለምሳሌ sēo sunne /ሴዮ ሱነ/ (ፀሐይቱ) አንስታይ፣ se mōna /ሴ ሞና/ (ጨረቃው) ተባዕታይ፣ þæt wæter /ት ዋተር/ (ውኃው) ግዑዝ ነበር።

ጽሕፈት

ቋንቋው መጀመርያ ፉሶርክ በተባለው የ ሩን ፊደል ሲጻፍ ክርስትና ከተቀበለ በኋላ ግን በ ላቲን አልፋቤት ሊጻፍ ጀመረ። አንዳንድ ተጨማሪ ፈደላት እንዲህ ነበሩ:

  • ȝ - ይህ ፊደል (ከ አይርላንድኛ ገብቶ) እንደ 'ይ' ወይም 'ግ' ወይም 'ኅ' ሊጠቀም ይችል ነበር።
  • ð - ይህ ፊደል ከላቲን d ተቀይሮ እንደ '' ወይም '' ሊጠቀም ይችል ነበር።
  • þ - ይህ ከቀድሞው ፉሶርክ ተገኝቶ ደግሞ እንደ '' ወይም '' ጠቀመ።
  • ƿ - ' W' የሚለው ፊደል ገና ስላልኖረ 'ው' ለመጻፍ በዚህ ፊደል (ከፉሶርክ ተገኝቶ) ነበር። በኋላ ዘመን ከ p (ፕ) ጋር ስላለው ተመሳሳይነት ይህ ፊደል ጠፋ። ስለዚህ የዛሬ ሊቃውንት ጥንታዊ እንግሊዝኛ የሚጽፉት በዘመናዊው 'w' ነው።
Other Languages
Ænglisc: Ænglisc spræc
asturianu: Inglés antiguu
беларуская (тарашкевіца)‎: Стараангельская мова
brezhoneg: Hensaozneg
català: Anglès antic
čeština: Staroangličtina
Deutsch: Altenglisch
English: Old English
français: Vieil anglais
Frysk: Aldingelsk
Հայերեն: Հին անգլերեն
Bahasa Indonesia: Bahasa Inggris Kuno
íslenska: Fornenska
日本語: 古英語
한국어: 고대 영어
Limburgs: Aajdingels
latviešu: Senangļu valoda
Bahasa Melayu: Bahasa Inggeris Kuno
Plattdüütsch: Angelsassische Sprake
Nederlands: Oudengels
norsk nynorsk: Gammalengelsk
occitan: Anglosaxon
português: Inglês antigo
srpskohrvatski / српскохрватски: Staroengleski jezik
Simple English: Old English
slovenčina: Anglosaština
slovenščina: Stara angleščina
svenska: Fornengelska
Türkçe: Eski İngilizce
Tiếng Việt: Tiếng Anh cổ
West-Vlams: Oudiengels
中文: 古英语
Bân-lâm-gú: Kó͘ Eng-gí
粵語: 古英文