ግዕዝ

ኦሪት ፡ ዘፍጥረት ፡ ፳፱ ፡ በግዕዝ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ

ግዕዝ ፡ በአፍሪካ ቀንድ ፡ በኢትዮጵያና ፡ በኤርትራ ፡ በጥንት ፡ የተመሠረተና ፡ ሲያገለግል ፡ የቆየ ፡ ቋንቋ ነው። የግዕዝ ፡ አመጣጥ ፡ በግምት ፡ የዛሬ ፡ ፫ ፡ ሺህ ፡ ዓመት ፡ ከየመን ፡ እና ፡ ደቡብ ፡ አረቢያ ፡ በመነሣትና ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ በመሻገር ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከሰፈሩ ፡ የተለያዩ ፡ የሳባውያን ፡ ነገዶች ፡ ቋንቋና ፡ በጊዜው ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ይነገሩ ፡ በነበሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ ዘገምተኛ ፡ ውኅደት ፡ ነው።[1] በአክሱም ፡ መንግሥትና ፡ በኢትዮጵያ ፡ መንግሥት ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነበር።

ግዕዝ ፡ ከአማርኛና ፡ ሌሎች ፡ ኢትዮ-ሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ጋር ፡ ሲወዳደር ፡ «ንጹሕ» ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው።[1] ግዕዝ ፡ እስከ ፡ ፲ኛው ፡ ክፍለ-ዘመን ፡ መጀመሪያ ፡ ድረስ ፡ ዋነኛ ፡ የመግባቢያ ፡ ቋንቋና ፡ ልሳነ ፡ ንጉሥ ፡ ነበር።[1] ከ ፲፫ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ጀምሮ ፡ ግን ፡ ሙሉ ፡ በሙሉ ፡ መነገር ፡ አቁሞ ፡ በሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ በትግርኛ ፡ እንዲሁም ፡ በማዕከላዊው ፡ ክፍል ፡ ደግሞ ፡ በአማርኛ ፡ ተተካ።[1] ዛሬ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሥነ-ስርዓት ፡ እንዲሁም ፡ በኤርትራ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፣ በኢትዮጵያ ፡ ካቶሊክ ፡ ቤተክርስቲያን እና ፡ በቤተ-እስራኤል ፡ ሥነ-ስርዓቶች ፡ ይሰማል።

ቋንቋው ፡ የሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ አባል ፡ እየሆነ ፡ በደቡብ ፡ ሴማዊ ፡ ቅርንጫፍ ፡ ውስጥ ፡ ይካተታል። ደቡብ ፡ ሴማዊ ፡ በመባሉ ፡ ግዕዝ ፡ የሣባ ፡ ቋንቋ ፡ ቅርብ ፡ ዘመድ ፡ ነው። ግዕዝ ፡ የተጻፈው ፡ በግዕዝ ፡ ፊደል ፡ አቡጊዳ ፡ ነው። ይህም ፡ ፊደል ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ለአማርኛ ፣ ለትግርኛ ፡ እና ፡ ለሌሎችም ፡ ቋንቋዎች ፡ ይጠቀማል። በመላውም ፡ የአፍሪቃ ፡ አህጉር ፡ ውስጥ ፡ የመጀመሪያውና ፡ ብቸኛ ፡ አፍሪቃዊ ፡ የራሱን ፡ ፊደላት ፡ የያዘ ፡ ቋንቋ ፡ ሲሆን ፣ በዓለምም ፡ ላይ ፡ ዋናና ፡ የስልጣኔ ፡ አራማጅ ፡ ከሚባሉት ፡ ቋንቋዎች ፡ አንዱ ፡ ነው።

በግዕዝ ፡ ጽሕፈት ፡ ፳፮ ፡ ፊደላት ፡ ብቻ ፡ ይጠቀሙ ፡ ነበር ፤ እነርሱም፦

፣ ኀ ፣ ፣ ጰ ፣ ፣ ፐ

ናቸው።

ሊቁ ፡ ሪቻርድ ፓንኩርስት ፡ እንደሚጽፍ ፣ አንድ ፡ ተማሪ ፡ በመጀመርያው ፡ አመት ፡ ፊደሉን ፡ ከተማረ ፡ በኋለ ፣ በሚከተለው ፡ አመት ፡ መጀመሪያይቱ ፡ የሐዋርያው ፡ የዮሐንስ ፡ መልእክትን ፡ ከአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግዕዝ ፡ ከትዝታ ፡ ለመጻፍ ፡ መማር ፡ ነበረበት። በሦስተኛው ፡ ደረጃ ፡ የሐዋርያት ፡ ሥራ ፡ በአራተኛውም ፡ መዝሙረ ፡ ዳዊት ፡ በግዕዝ ፡ ማስታወስ ፡ ነበረበት። ይህንን ፡ ከጨረሰ ፡ ታላቅ ፡ ግብዣ ፡ ይደረግና ፡ ልጁ ፡ ጸሐፊ ፡ ይሆን ፡ ነበር።

በብሪቲሽ ፡ ቤተ-መጻሕፍት ፡ (የእንግሊዝ ፡ አገር ፡ ብሔራዊ ፡ ቤተ-መጻሕፍት) ፡ ውስጥ ፡ ፰፻ ፡ የሚያሕሉ ፡ የድሮ ፡ ግዕዝ ፡ ብራናዎች ፡ አሉ።

በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ፡ ትምህርቶች ፡ ዘንድ ፣ ግዕዝ ፡ የአዳምና ፡ የሕይዋን ፡ ቋንቋ ፡ ነበር። ፊደሉን ፡ የፈጠረው ፡ ከማየ አይኅ ፡ አስቀድሞ ፡ የሴት ፡ ልጅ ፡ ሄኖስ ፡ ነበረ። ከባቢሎን ፡ ግንብ ፡ ውድቀት ፡ በኳላ ፣ ከአርፋክስድ ፡ ወገን ፡ የዮቅጣን ፡ ልጆች ፡ ቋንቋውን ፡ እንደ ፡ ጠበቁት ፡ ይባላል። የዮቅጣን ፡ ልጅ ፡ ሣባ ፡ ነገዶች ፡ ከዚያ ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ አሻግረው ፡ ወደ ፡ ዛሬው ፡ ኢትዮጵያ ፡ ያስገቡት ፡ ይታመናል። እንዲሁም ፡ ካዕብ ፡ እስከ ፡ ሳብዕ ፡ (አናባቢዎችን ፡ ለመለየት) ፡ ወደ ፡ ፊደል ፡ የተጨመረበት ፡ ወቅት ፡ በንጉሥ ፡ ኤዛና ፡ ዘመን ፡ እንደ ፡ ነበር ፡ ይባላል።

Other Languages
Afrikaans: Ge'ez
aragonés: Idioma ge'ez
العربية: لغة جعزية
مصرى: جعزى
български: Геез
brezhoneg: Geuzeg
català: Gueez
čeština: Ge'ez
dansk: Ge'ez
English: Geʽez
Esperanto: Geeza lingvo
español: Ge'ez
euskara: Ge'ez
فارسی: زبان گعز
français: Guèze
galego: Lingua ge'ez
עברית: געז
हिन्दी: गिइज़ भाषा
hrvatski: Geez
Bahasa Indonesia: Bahasa Ge'ez
italiano: Lingua ge'ez
日本語: ゲエズ語
ქართული: გეეზი
한국어: 그으즈어
Кыргызча: Эфиоп тили
lietuvių: Gezo kalba
македонски: Гиз
മലയാളം: ഗീയസ് ഭാഷ
Bahasa Melayu: Bahasa Ge'ez
Nederlands: Ge'ez
norsk nynorsk: Geez
norsk: Geez
occitan: Gueez
polski: Język gyyz
Piemontèis: Lenga Geez
português: Língua ge'ez
română: Limba gî'îz
русский: Геэз
srpskohrvatski / српскохрватски: Giz
slovenščina: Giz
српски / srpski: Гиз (језик)
svenska: Ge'ez
Kiswahili: Kige'ez
Türkçe: Geez dili
українська: Ґеез
اردو: گعز
oʻzbekcha/ўзбекча: Efiop tili
Tiếng Việt: Tiếng Ge'ez
中文: 吉茲語
粵語: 吉茲文