ኡቱ-ኸጛል

ኡቱ-ኸጛልኡሩክና የ ሱመር ንጉሥ ነበር። በ1985 ዓክልበ. ግድም የ ጉታውያንን መጨረሻ ንጉሥ ቲሪጋንን ማረከና ጉታውያንን ከሱመር አስወጣቸው። ስለዚህ ኡሩክ የሱመር ላዕላይነት ያዘ። በ ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር በአብዛኛው ቅጂ 427 ዓመታት እንደ ገዛ ሲል ሌሎች ቂጂዎች 27 ዓመታት ወይም 7 ዓመታት ይላሉ። ሆኖም ከኡቱ-ኸጛል የዓመት ስሞች አንድ ብቻ ይታወቃል፣ እሱም «ኡቱ-ኸጛል ንጉሥ የሆነበት ዓመት» ይባላል። ስለዚህ ከአንድ አመት በላይ ብዙ እንደ ቀረ አጠያያቂ ነው። ከ ኡር አለቃ ኡር-ናሙና ከ ላጋሽ አለቃ ናማሐኒ መካከል አንድ ጸብ ተነሥቶ ኡቱ-ኸጛል ክርክሩን ለላጋሽ አደለ። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግን ኡር-ናሙ የሱመር ላዕላይ ንጉሥ ሆነ። በአንድ ሰነድ ዘንድ ኡቱ-ኸጛል አንዱን መስኖ ገደብ በመመርመር እያለ በወንዙ ወድቆ ሰመጠ። በ ዋይድነር ዜና መዋዕል በተባለ ጽላት ኡቱኸጛል «የተቀደሠውን ከተማ» ባቢሎንን ስለ ወነጀለ የጠፋ ነው።

ቀዳሚው
ቲሪጋን
ሱመር ነጉሥ
1985-1984 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኡር-ናሙ
Other Languages
العربية: أوتو حيكال
català: Utukhengal
Deutsch: Utuḫengal
English: Utu-hengal
español: Utu-hegal
français: Utu-hegal
עברית: אותו-ח'גל
magyar: Utu-héngál
Bahasa Indonesia: Utu-hengal
italiano: Utukhegal
Kurdî: Utu-hengel
polski: Utuhengal
português: Utuhengal
русский: Утухенгаль
srpskohrvatski / српскохрватски: Utu-hegal
српски / srpski: Уту-Хенгал
Türkçe: Utu-hegal
українська: Утухенгаль