ሳይንሳዊ ዘዴ

"ብርሃን በአስተላላፊወች ዘንድ በቀጥታ መስመር ይጓዛል" — አላዝን ስነ ብርሃን በተሰኘ መጽሃፉ (1021).

ሳይንስ ከሌሎች የዕውቀት ዘርፎች (ለምሳሌ ፍልስፍና ወይም ሂሳብ ወይም ስነ ሃይማኖት) የሚለይበት ዋናው ቁም ነገር የሳይንስ ዘዴን በመጠቀሙ ነው። እርግጥ ነው ። ሳይንሳዊ ዘዴ ተብሎ የሚታወቀው ስርዓት ብዙ ጊዜ በዝርዝር ድረጃ በድረጃ በሚከተለው መልኩ ሲቀርብ እናያለን፦

  1. ስለሚታየው አለም "ጥያቄ" አንሳ። ሁሉም የሳይንስ ስራ የሚጀምረው ጥያቄ በማቅረብ ነው። ትክክለኛና በ"ተመክሮ" ሊመለስ የሚችል ጥያቄ የማቅረብ ችሎታ እንደ ትልቅ የሳይንስ ጥበብ ይቆጠራል።
  2. ለጥያቄህ መልስ ሊሆን የሚችል "መላ ምት" ፍጠር። "መላ ምት" ማለት የግምት አይነት ሲሆን እንዲሁ በዘፌቀደ የሚደረግ ግምት ሳይሆን ያለፈን ተመክሮ እና ትምህርትን ያገናዘበ ነው። በተረፈ ይህ መላ ምት እውነት ወይም ውሽት መሆኑ ሊረጋገጥ የሚችል መሆን አለበት። ለምሳሌ "ሰማያዊ ቀለም ከቀይ ቀለም የተሻለ ነው" የሚል አስተሳሰብ "ሳይንሳቂ መላ ምት" ሊሆን አይችልም ምክንያቱም እውነት ይሁን ውሽት ማረጋገጥ ስለማይቻል። ነገር ግን ለምሳሌ "ሰማያዊ ቀለምን የሚወድ የሰው ብዛት ቀይ ቀለምን ከሚወደው ይበዛል።" ይህ "ሳይንሳዊ መላምት ሊሆን ይችላል ምክንያቱም እውነት ይሁን ውሸት ሰወችን በመሰብሰብ እና በመጠየቅ በተሞክሮ ማረጋገጥ ይቻላልና።
  3. መላ ምትህን ሊፈትን የሚችል ሙከራ ዘይድ። እውነተኛ ሳይንሳዊ መላምት በሙከራ ሊፈተን የሚችል ነው። በሙከራ ሊፈተን ካልቻለ በርግጥም ሳይንሳዊ አይደለም። ከዚህ በተረፈ፣ ሙከራው የመላምቱን ውሸትነት ሊያረጋግጥ ይችላል፣ እውነቱነቱን ግን ሊናገርም ላይናገርም ይችላል። ለምሳሌ አንድ መኪና አልነሳ ቢል፣ በሳይንሳዊ መንገድ ጥያቄ መጀመሪያ እናቀርባለን "ለምንድን ነው ያልተነሳው?" መላ ምታችን "ባትሪው ስላለቀ ነው" ይሆናል። ይህን መላምት ለመፈተን የባትሪውን አቅም በቮልት ሜተር እንድንለካ የሙከራ አቅድ እናወጣለን። ባትሪውን ስንለካ ሃይሉ ሳይሟጠጥ ካገኘነው በርግጥም መላምታችን ስህተት መሆኑን በሙከራ አረጋገጥን ማለት ነው። ባትሪው ሃይሉ ተሟጦ ካገኘነው ግን መላምታችን ትክክል መሆኑን አያሳይም ምክንያቱም መኪናው ሌላም ችግር ሊኖርበት ይችላልና። ለምሳሌ "ስታርተሩ" ላይሰራ ይችላል። ስለዚህ ሙከራ አንድን የሳይንስ መላምት ውሽትነት ማረጋገጥ ቢችልም እውነትነቱን ግን አያረጋግጥም።
  4. ሙከራህን አካሂድ በዚያውም መረጃ ሰብስብ።
  5. ከሙከራህ ተነስተህ ድምዳሜ ላይ ድረስ። በርግጥ ያቀረብከው መላምት ውሽት መሆኑን ሙከራህ ያሳያል? ካላሳየ መላምትህ ለጊዜው (በሌላ ሙከራ እስካልተስባበለ ድረስ) ልክ ነው ማለት ነው። ውሽት መሆንኑን ካረጋገጥክ ከጀረጃ 2 ጀምረህ እንደገና ሞክር።
  6. ድምዳሜህንና መላምትህን ለሌሎች አስታውቅ። ይህ ደረጃ ሳይንቲስቶች የጋን መብራት እንዳይሆኑ ከማገዱም በላይ ያንድን ሰው መላምቶችና ተመክሮወች በሌሎች ሳይንቲስቶች እንዲመዘን እና እንዲረጋገጥ መንገድ ይከፍታል።

እነዚህ እርከኖች በርግጥ ሁልጊዜ በሁሉ ሳይንቲስት የሚደረጉ ባይሆን፣ ነገር ግን ባጠቃላይ መልኩ ስለዓለማችን አስተማማኝ ሃቆችን ለማግኘት የሚረዱ መሆናቸው ይታመንባቸዋል።

እምነትና ተጨባጭ ሃቅ

ተንሳፋፊ ግልቢያ፣ ውሽትነቱ የተረጋገጠ የተንሻፈፈ እምነት

ሰዎች በአንድ ነገር ላይ ያላቸው እምነት የሚያዩትን ነገር ሁሉ አንሻፈው እንዲገነዘቡ ሊያስገድዳቸው ይችላል። ስር የሰደደ ግን ተጨባጭነት የሌለው እምንተ፣ በሌሎች ተቃውሞ ቢደርስበት እንኳ ባለቤቱ እስከመጨረሻው ሙጥኝ ሊለው ይችላል።

ተማሪዎች በምርምር እንደደረሱበት፣ ብዙ ሰዎች በነገሮች ላይ ያላቸው የመጀመሪያ እይታ ትክክለኛነት ይጎድለዋል። ሁለተኛና ሶስተኛ ጊዜ የተደገመ የተሞክሮ እይታ፣ ለሃቅ ቀርብ ይላል። ከአንድ ተመክሮ ላይ እውነተኛው ሃቅ የመውጣቱ ወይም እስከመጨረሻው የመደበቁ ምስጢር ተመክሮውን በሚያደርገው ሰው የአእምሮ ክፍትነት፤ ልምድ፣ በ ራስ መተማመን፣ ጊዜ፣ እና ምቾት ላይ ይመሰረታል [1]

ኢድወርድ ሙይብሪጅ የፈረስን ኮቴ አረማምድ በእርግጥ እንዳሳየ

በድሮ ቻይናዎች እና አውሮጳ ሰዓሊዎች ዘንድ፣ የሚጋልቡ ፈረሶች እግሮቻቸው ተበልቅጠው ይታያሉ። ይሄ እንግዲህ ሰዓሊዎቹ ስለ ፈረሶች ኮቴ ከነበራቸው እምነት የመጣ እንጂ በርግጥም በተፈጥሮ የሚገኝ ጉዳይ/ሃቅ አልነበረም። ኤድዋርድ ሞይብሪጅ የሚጋብን ፈረስ ተንቀሳቃሽ ስዕል በመቅረጽ እና ቅጽበት በቅጽበት በመመርመር ከላይ የተጠቀሰው እምነት ውሸት እንደሆነ አሳየ። በዚህ ምርምር መሰረት፣ ሁሉም የፈረስ ሸኮናዎች መሬትን ሲለቁ፣ ከመበልቀጥ ይልቅ ፣ አንድ ላይ የመሰብሰብን ሁኔታ እንደሚያሳዩ ታወቀ።

ስለሆነም በሳይንሳዊ ዘዴ አካሄድ፣ መላምቶች ምንጊዜም እንዲፈተኑ ስለሚያጠይቅ፣ የተንሻፈፉ እምነቶች (ለምሳሌ የሚንሳፈፍ ግልቢያ) ከአንድ ግለሰብም ሆነ ህብረተሰብ አዕምሮ ውስጥ ተነቅለው እንዲዎጡ ይረዳል።

Other Languages
беларуская: Навуковы метад
беларуская (тарашкевіца)‎: Навуковы мэтад
български: Научен метод
bosanski: Naučna metoda
čeština: Vědecká metoda
Esperanto: Scienca metodo
فارسی: روش علمی
հայերեն: Մեթոդ
interlingua: Methodo scientific
Bahasa Indonesia: Metode ilmiah
Interlingue: Method scientific
日本語: 科学的方法
Taqbaylit: Tarrayt tusnant
қазақша: Ғылыми әдіс
한국어: 과학적 방법
македонски: Научен метод
Bahasa Melayu: Kaedah saintifik
नेपाल भाषा: वैज्ञानिक तवः
norsk nynorsk: Vitskapleg metode
Norfuk / Pitkern: Saientifik methud
srpskohrvatski / српскохрватски: Naučna metoda
Simple English: Scientific method
slovenčina: Vedecká metóda
slovenščina: Znanstvena metoda
српски / srpski: Naučna metoda
українська: Науковий метод
中文: 科学方法
粵語: 科學方法