ሙሴዎን

የእስክንድርያ መጻሕፍት ቤት

ሙሴዎንእስክንድርያግብጽ በግሪኮች ፈርዖን ፩ በጥሊሞስ የተመሠረተ ጥንታዊ የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተቋም ነበር። ምናልባት ከ300 ዓክልበ. ግድም እስከ 264 ዓም. ድረስ ቆየ።

ዝነኛው የእስክንድርያ መጻሕፍት ቤት በዚህ ውስጥ ተገኘ። መጻሕፍት በማንኛውም ቋንቋ ከግሪክ አገር፣ ይሁዳ፣ መስጴጦምያፋርስሕንድ ወዘተ. ተከማችተው ተተረጎሙ።

በተቋሙ ውስጥ ከተማሩት ጥናቶች መካከል በተለይ ሙዚቃቅኔፍልስፍናሥነ አካልሥነ ፈለክና ሌላ የሳይንስ ዕውቀት ነበሩ።

ምናልባት አንድ ሺህ ተማሮች ሲኖሩበት የተማሮችና የአስተማሮች ውጪ ሁሉ በፈርዖን መንግሥት ተደገፈ። መኖሪያ፣ መብልና አልገልጋይ ቢሆንም በነጻ ተቀበሉ። ይህ ኩሁሉ ጎበዝ ለሆኑት ተማሮች ነበረ።

በሙሴዎን ተቋም ታዋቂ ከሆኑት ተማሮች መካከል፦

  • አርኪሜዴስ - ሒሳብ ተመራማሪና 'የምህንድስና አባት'
  • አሪስታርኮስ ዘሳሞስ - መጀመርያ ማዕከለ ፀሐይ አስተያየት አቀረበ
  • ካሊማቆስ - የታወቅ ባለቅኔ፣ ሃያስና መምህር
  • ኤራሲስትራቶስ - ሐኪምና ከሄሮፊሎስ ጋር የእስክንድርያ ሕክምና አካዳሚ መሥራች
  • ኤራቶስጤኔስ - ምድር ሉል እንደ ነበረች፣ ስፋቷን በትክክል አሰላ
  • ዩክሊድ - 'የጂዎሜትሪ አባት' ይባላል።
  • ሄሮፊሎስ - ታዋቂ ሐኪም፣ የሳይንሳዊ ዘዴ መስራች
  • ሂፓርቆስ - የትሪጎኖሜትሪ መስራች
  • ፓፖስ ዘእስክንድርያ - የሂሳብ ተመራማሪ
  • ሄሮን ዘእስክንድርያ - 'የመካኒካ አባት'

ሮሜ መንግሥት ዘመን፣ ተቋሙ በቄሣሮች ድጋፍ እስከ 264 ዓም ይቀጥል ነበር። በዚህ ዘመን በመላው ሮሜ መንግሥት ውስጥ ሌላ ከፍተኛ ትምህርት ቤት አልነበራቸውም። በአብዛኛው በሮማውያን ዘንድ ትምህርት የተገኘው ከግል መምህር ነበርና። ሙሴዎን በቄሣሩ አውሬሊያን ትዕዛዝ በ264 ዓም እንደ ተቃጠለ ይመስላል።

የ«ሙሴዎን» ስም ከግሪክ አፈ ታሪክ ሲሆን ከኢትዮጵያ የወጡትን ዘጠኝ «ሙሳዮች» (ሴት ዘፋኞች) ለማክበር ተሰየመ። በዘመናዊ ልሳናት ደግሞ «ሙዚየም» (በተ-መዘክር) ከዚህ ተቋም ስም ደረሰ።

Other Languages
مصرى: موسيون
azərbaycanca: Museyon
български: Музейон
English: Musaeum
español: Museion
eesti: Museion
euskara: Museion
suomi: Museion
עברית: מוזאיון
hrvatski: Museion
Bahasa Indonesia: Mouseion
日本語: ムセイオン
한국어: 무세이온
Nederlands: Mouseion
norsk: Museion
srpskohrvatski / српскохрватски: Museion
svenska: Museion
oʻzbekcha/ўзбекча: Aleksandriya museyoni